Job 26

ኢዮብ

1ኢዮብም እንዲህ ሲል መለሰ፤

2“ኀይል የሌለውን ምንኛ ረዳኸው!
ደካማውንስ ምንኛ አዳንኸው!
3ጥበብ የሌለውን ምንኛ መከርኸው!
ታላቅ ዕውቀትንስ ምንኛ ገለጥህለት!
4ይህን ቃል እንድትናገር የረዳህ ማን ነው?
የማንስ መንፈስ በአንደበትህ ተጠቀመ?

5“ከውሆችና በውስጣቸው ከሚኖሩ በታች ያሉ፣
የሙታን መንፈስ በጭንቅ ላይ ናቸው።
6ሲኦል
የዕብራይስጡ ቅጅ ከዚህ ጋር ይስማማል፤ አንዳንድ ቅጆች ግን፣ ሞት ይላሉ።
በእግዚአብሔር ፊት ዕራቍቷን ናት፤
የጥፋትንም
ዕብራይስጡ፣ አባዶን ይላል።
ስፍራ የሚጋርድ የለም።
7የሰሜንን ሰማይ በሕዋው ላይ ዘረጋው፤
ምድርንም እንዲያው በባዶው ላይ አንጠለጠላት።
8ውሆችን በደመናዎቹ ይጠቀልላል፤
ክብደታቸውም ደመናዎቹን አይሸነቍርም።
9ደመናዎቹን በላዩ ዘርግቶ፣
የሙሉውን ጨረቃ ፊት ይጋርዳል።
10ለብርሃንና ለጨለማ ድንበር ይሆን ዘንድ፣
በውሆች ላይ የአድማስ ክበብ አበጀ።
11የሰማይ ምሰሶዎች ይንቀጠቀጣሉ፤
በተግሣጹም ይደነግጣሉ።
12በኀይሉ ባሕርን ያናውጣል፤
በጥበቡም ረዓብን ይቈራርጣል።
13በእስትንፋሱ ሰማያትን አጠራ፤
እጁም ተወርዋሪውን እባብ ወጋች።
14እነዚህ የሥራው ዳር ዳር ናቸው፤
ስለ እርሱ የሰማነው ምንኛ አነስተኛ ነው!
የኀይሉንስ ነጐድጓድ ማን ሊያስተውል ይችላል?”
Copyright information for AmhNASV